ጳጉሜ አንድ የአገልግሎት ቀንን አስመልክቶ በድሬዳዋ በመንግሰስት ተቋማት በሴክተር እና በወረዳ ባማረና በደመቀ ሁኔታ ተገልጓዮች አገልግሎት እያገኙ ይገኛል።
በዛሬው እለትም እለቱን ምክንያት በማድረግ የምሳ ሰአት ጭምር አገልግሎት እንደሚሰጡ ተዘዋውረን በተመለከትናቸው ተቋማት ገልፀዋል።
ቀኑን በማስመልከትም በአስተዳደሩ በከተማው ስጥ ነፃ የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት፣በጤና ተቋማት ያለምንም ክፍያ የህክምና አገልግሎት እንዲሁም ነዋሪው ማህበረሰብ በከተማው በተለያዩ ቦታዋች እና አገልግሎት ሊያገኝ በሄደባቸው ወረዳዋች የጤናቸውን ሁኔታ የሚያረጋግጥበት የህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።
በትዕግስት ቶሎሳ
ፎቶ፦ ሰላም አበበ