ጷግሜን ለኢትዮጲያ በሚል መሪ ሀሳብ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት የጷግሜ ቀናት በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ይከበራሉ ። በዛሬው እለትም ጷግሜ 1 የአገልግሎት ቀን “ኢትዮጵያን እናገልግል ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ሲሆን በአሁኑ ሰአትም በድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን አዘጋጅነት በቀድሞው መናሀሪያ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ቀኑን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ መርሀ-ግብሮች እየተከበረ ይገኛል ።
በዚሁ መርሀ ግብር ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ፣ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ዋና ስራ-አስኪያጅ ወሮ ሰአዳ አዋሌ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሆነዋል ።
በአለማየሁ አበበ ።